ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍሳችን እረኛ ነው። የጌታ ቃል እንደሚነግረን እኛ በክርስቶስ የሆንን አዲስ ፍጥረት ነን፡ አሮጌው ነገር አልፏል። ስለሆነም በአሮጌው ማንነታች እዉስጥ የነበሩ ለምሳሌ እንደ ይቅርታ አለማድረግ፣ ትክክለኛ ያልሆነ የፍርድ ቃል ማውጣትና ሌሎች የተለያዩ ሰይጣን ከሚጠቀምባቸዉ እስራቶችና ቀንበሮች ነፃ በመዉጣት ክርስቶስ በከፈልን ነፃነት እንድንኖር የእግዚአብሔር ፍፁም ፈቃዱ ነው። ይህንንም ለውጥ በህይወታችን እንዲመጣ እኛ በሙሉ ፈቃዳችን ተሰጠን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመተባበርና በእርሱ ሀይል መውጣት ያለበትን አሮጌውን ማንነታችንንና በልባችን ውስጥ ያሉ ቆሻሻዎችን በማስወገድ ለመንፈስ ቅዱስ በልባችን ዉስጥ ቦታ በመስጠት ነዉ። የውስጥ ፈውስ (Inner Healing) በሚል የሚዘጋጀዉ ፕሮግራም ይህንኑ ሥራ ይሰራል። በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በመታገዝ በጥልቀት ነፍሳችንን በመመርመር በመንገዳችን ላይ ያሉ ተግዳሮችን አንድ በአንድ በማስወገድ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ በሙላት እንዲቀሳቀስ ይረዳል።
ፕሮግራሙ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች
ከእግዚአብሔር ያልሆኑ እምነቶች
መራራ ሥርና ይቅርታ ያለማድረግ መዘዞች
ፍርድ
ከባድ የህይወት አጋጣሚዎች
ድብቅ ቃለመሃላዎች
የዘር ሀረግ እርግማኖች
ይመዝገቡ
ይህ ትምህርት የሚካሄደው ለተከታታይ 3 ቀናት በጥንቃቄ በተመረጠ ቦታ ሲሆን ከ10 – 20 ሰዎች የሚያሳትፍ ይሆናል።
በነዚህ ቀናት ውስጥ የሚቀስሙት መንፈሳዊ ዕውቀት ህይወትዎን ከመቀየር ባሻገር ከእግዚአብሔር ጋር ያሎትን አካሄድ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ያሳድግሎታል፤ እርሶ ነፃ ወጥተው ለሌሎች በአካባቢው ያሉት ሰዎች መዳን ምክንያት እንዲሆኑ ይታጠቃሉ።
ማሳሰቢያ: ይህ የኢነር ሂሊንግ ፕሮግራም የሚሰጠው በነፃ ነዉ። የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን የማደርያ እና የምግብ ዋጋን ይሸፍናል።
ምስክርነቶች
አድራሻ
ስልክ ቁጥር
+251 991 188027
የኢሜይል አድራሻ
innerhealing@gmail.com