Skip to main content

የውስጥ ፈውስ በኢትዮጵያ

የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አገልግሎት

 

የውስጥ ፈውስ መርሃግብር

ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍሳችን እረኛ ነው። የጌታ ቃል እንደሚነግረን እኛ በክርስቶስ የሆንን አዲስ ፍጥረት ነን፡ አሮጌው ነገር አልፏል። ስለሆነም በአሮጌው ማንነታች እዉስጥ የነበሩ ለምሳሌ እንደ ይቅርታ አለማድረግ፣ ትክክለኛ ያልሆነ የፍርድ ቃል ማውጣትና ሌሎች የተለያዩ ሰይጣን ከሚጠቀምባቸዉ እስራቶችና ቀንበሮች ነፃ በመዉጣት ክርስቶስ በከፈልን ነፃነት እንድንኖር የእግዚአብሔር ፍፁም ፈቃዱ ነው። ይህንንም ለውጥ በህይወታችን እንዲመጣ እኛ በሙሉ ፈቃዳችን ተሰጠን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመተባበርና በእርሱ ሀይል መውጣት ያለበትን አሮጌውን ማንነታችንንና በልባችን ውስጥ ያሉ ቆሻሻዎችን በማስወገድ ለመንፈስ ቅዱስ በልባችን ዉስጥ ቦታ በመስጠት ነዉ። የውስጥ ፈውስ (Inner Healing) በሚል የሚዘጋጀዉ ፕሮግራም ይህንኑ ሥራ ይሰራል። በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በመታገዝ በጥልቀት ነፍሳችንን በመመርመር በመንገዳችን ላይ ያሉ ተግዳሮችን አንድ በአንድ በማስወገድ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ በሙላት እንዲቀሳቀስ ይረዳል።

ለበለጠ መረጃለበለጠ መረጃ

በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል፡ ብሎ ጮኸ

ዮሐንስ 7፡38

ፕሮግራሙ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች

ከእግዚአብሔር ያልሆኑ እምነቶች

መራራ ሥርና ይቅርታ ያለማድረግ መዘዞች

ፍርድ

ከባድ የህይወት አጋጣሚዎች

ድብቅ ቃለመሃላዎች

የዘር ሀረግ እርግማኖች

ይመዝገቡ

ይህ ትምህርት የሚካሄደው ለተከታታይ 3 ቀናት በጥንቃቄ በተመረጠ ቦታ ሲሆን ከ10 – 20 ሰዎች የሚያሳትፍ ይሆናል።
በነዚህ ቀናት ውስጥ የሚቀስሙት መንፈሳዊ ዕውቀት ህይወትዎን ከመቀየር ባሻገር ከእግዚአብሔር ጋር ያሎትን አካሄድ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ያሳድግሎታል፤ እርሶ ነፃ ወጥተው ለሌሎች በአካባቢው ያሉት ሰዎች መዳን ምክንያት እንዲሆኑ ይታጠቃሉ።

ማሳሰቢያ: ይህ የኢነር ሂሊንግ ፕሮግራም የሚሰጠው በነፃ ነዉ። የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን የማደርያ እና የምግብ ዋጋን ይሸፍናል።

ምስክርነቶች

በውስጣዊ ፈውስ ውስጥ ያጋጠሙኝ ልምዶች በጣም ጥልቅ ናቸው ፡፡ ወደ ሁሉም ጉዳት እና ተስፋ መቁረጥ በጥልቀት ለመሄድ እድል አግኝቼ ነበር እናም ሰዎችን ይቅር ለማለት እና ሁኔታዎችን ለመርሳት ችያለሁ ፡፡ ታላቅ መዳን ነበር እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሁሉንም ማስተዋል በሚያልፈው ሰላም እየተደሰትን ነው እናም ሁሉም ሰው ሊያልፍበት የሚገባ ግኝት እንደሆነ አምናለሁ ፡፡

Freyhiwot

ሻሎም ወገኖቼ ሁሉ መልካም ነው ? እኔ ክብር ለስሙ ይሁን ደህና ነኝ፡፡ ወገኖቼ የእድሜ ልክ ጥዬቄ በ3ቀን ትምህርት ተፋታልኝ፡፡ ለኔ ትምህርቱ ሄይወቴን ነው የቀየረው እራሴን እንዳይ ረድቶኛል፡፡ ረጂም ወራት እንቅልፍ አልተኛም ነበር፣ ምክንያቱም በልቤ በጣም ብዙ የሚያስጨንቀኝ ና ተናግሬም የማይወጣልኝ ትልቅ ችግር እና ጭንቀት ውስጥ ነበርኩ፡፡ ?ዛሬ አዲስ ቀን ነው ምክንያቱም ከተማርኩት ትምህርት የተነሳ በጣም ደስ የሚልና ብዙ ለውጥ በህይወቴ ላይ ማየት ጀምሬአለሁ፡፡ ይቅርታ የፅድቃችን የህይወት ጋሻ፣ እንዲሁም የቂም ማርከሻ ፣የቃልኪዳን ማደሻ ነው፡፡ያለፈውን ሙሉ በሙሉ በመተው ዛሬ ላይ ከቤተሠቦቼ ጋር በመስማማት ፣ሰላማዊ ሊባል በሚችል መልኩ ፣ኑሮዬን እየኖርኩ ነው፡፡ እንዲሁም ካለብኝ የዘር ማንዘር መርገም ነፃ ሆኜ ፣በክርስቶስ እየኖርኩ ነው፡፡ይቅርታ ማረግ በረከትን ወደ ህይወትህ ማምጣት ቺያለሁ፡፡ በመጨረሻም ማለት ምፈልገው ትምህርቱ በኔ ህይወት ላይ በጣም ብዙ ለውጥ ያመጣ ቢሆንም ከብዙ በጥቂቱ ነው ለእናንተ ያካፈልኩት፡፡ እናንተም በመማር በእራሣችሁና በቤተሠባችሁ ላይ ለውጥን እንድታመጡ አበረታታችዓለሁ፡ ተባረኩ ?ሳራ የጌታ ነኝ

ስም-አልባ

ክብር ለእርሱ ፣ የውስጣዊውን ብጥብጥ ፈውስ ከተማርኩ በኋላ ፣ በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ለውጦች ከሆኑት አንዱ ፣ ባለፉት ዓመታት ውስጥ ከሶስት ዓመታት መራራ በኋላ ፣ ኢየሱስ አንዴ እና ለአንዴ ቀሰቀሰኝ

ስም-አልባ

የውስጠ-ፈውስ ክፍል አስደናቂ መንፈስን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መተባበርንና መተባበርን ፈጠረ ፡፡ እራስን መፈለግ እና ካለፈው ጋር ተስማምቶ መምጣት። ለምን እንደዚህ ሆነ? ከልጅነትዎ ጀምሮ በእርግዝና እስከ አዋቂነት ፣ መቀበል ፣ ቁስሎች መረዳትና መፈወስ።
እውነተኛው ክርስትና አዕምሮአችን እና አመለካከታችን በውስጣችን ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን እንዲኖር ማድረግ ነው ፡፡
ይቅር ባይ ነኝ? ፈራጅ ሆኛለሁ? ከክርስቶስ ጋር መኖር የመረረነትን እና ርካሽ የጎደለው መንገድ እና ሁሉንም የተሳሳቱ ስራዎች ንስሐ መመለስ ነው? ወደ ሙሉ ህብረት እና ከክርስቶስ ጋር መለያየት ሁሉንም መሰናክሎች ለማስወገድ የረዳኝ የፈውስ ሂደት ነው ፡፡
ከክፍል ጓደኞቻችን ጋር የህብረት ጊዜ ነበር ፡፡ አንዳችን ለሌላው ማስተማር እና ማረም ፣ አንዳችን ለሌላው ማበረታታት ፣ አንዳችን ለሌላው መጸለይ እና አንዳችን የሌላችንን ሸክም መሸከም እንዳለብን ተነግሮናል ፡፡ በትምህርት ክፍላችን መጨረሻ ላይ እርስ በርሳችን የምንወዳደድ እና በክርስቶስ አንድ ቤተሰብ ሆነናል ፡፡

Konjit Yilma

በውስጠ-ፈውስ ክፍለ ጊዜ ከገባሁበት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቅርብ የሆነ ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም .... የመንፈስ ቅዱስ መገኘቱ ተጨባጭ ነበር… አስደናቂው ተሞክሮ እግዚአብሔር ይባርከው ሴኔትን ፡፡

Mulu

አድራሻ

ስልክ ቁጥር

+251 991 188027

የኢሜይል አድራሻ

innerhealing@gmail.com

መልእክቶን ይፃፉ